top of page
Resized_20200419_021516.jpeg

አገልግሎት

OUR MINISTRIES

 

የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣እንደ አጽዋማት፣ ታላላቅ በዓላት እና የመሳሰሉትን መርሐግብሮች ጊዜውን ጠብቆ ፕሮግራም በማውጣት ሕዝቡን የሚያገለግል ሆኖ በተጨማሪም ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ዕለቱንና ሰዓቱን  ጠብቀው እንዲፈጽሙ መዘምራኑን፣ ልዑካኑንና ተጓዳኝ አገልጋዮችን የሚመራና የሚቆጣጠር የመንፈሳዊ አገልግሎት ክፍል ነው፡፡

20200418_232103.jpg
 

 

መንፈሳዊ አገልግሎት ምንድን ነው የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ መመለስ በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ የሚኖረንን ሚና ለማወቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ‹‹መንፈሳዊ (Spiritual)›› እና ‹‹አገልግሎት (Service)›› የሚሉትን ቃላቶች የያዘ ሲሆን ‹‹መንፈሳዊ›› የሚለው ገላጭ የአገልግሎቱን ዓላማና መሪ የሚያሳይ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው የሰው ልጆች ድኅነት ነው፡፡ መሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሰው ልጆች ለመንግስተ ሰማያት እንዲበቁ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ‹‹መንፈሳዊ አገልግሎት›› ሊባል ይችላል፡፡ ይህም የሕይወትን ቃል ያላወቁ ወገኖች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ማድረግ፣ ያመኑት ደግሞ እንዲጸኑና መንፈሳዊ ትሩፋትን እንዲሠሩ ማድረግን ያካትታል፡፡

የመንፈሳዊ አገልግሎት መሰረቱ በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድና ፈቃዱን ለመፈጸም የሚያተጋን አምላካዊ መመሪያ ነው፡፡ ከዘመነ አበው ጀምሮ፣ በዘመነ ኦሪትም በቅዱሳን አባቶችና ነቢያት አድሮ የመንፈሳዊ አገልግሎት ተልዕኮንና መመሪያን የሰጠው በፍፁም አንድነትና በልዩ ሦስትነት የሚመሰገን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከሦስቱ አካላት አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ግዕዘ ህፃናትን ሳያፋልስ በትህትና አድጎ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት ምን መምሰል እንዳለበት በተግባር አስተምሮ ለቅዱሳን ሐዋርያት አብነት የሆነ የአገልግሎት ተልዕኮና መመሪያ ሰጥቷቸዋል፡፡ አብነት የሆነው ተልዕኮ ‹‹እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ›› የሚለው ሲሆን መሪ መመሪያው ደግሞ ‹‹ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ›› የሚለው ታላቅ ቃል ነው  (ማቴ 10፡16)፡፡ ጌታችን ይህንን ተልዕኮና መመሪያ የሰጠው ለጊዜው ለደቀ መዛሙርቱ ሲሆን ኋላም በእነርሱ እግር ተተክተው በመንፈሳዊ አገልግሎት ለሚሳተፉ ሁሉ ነው፡፡

ቃጠሎ 9.jpg
ሰንበት ት/ቤት 
Sunday School

 

ሰንበት ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን እንዲያስቡ የተጻፈላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል የሚያምኑ እና የሚታመኑ ወጣቶች በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን ያስቡ ዘንድ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ ተጠሪነቱ ለሰበካ ጉባኤው ሆኖ የተደራጀ የወጣቶች የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር እና የጸሎት ማዕከል ነው፡፡

ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ስለ ቤተክርስቲያን አደረጃጀት እና መዋቅራዊ አሠራር፣ ስለ ክብረ ክህነት እና ስለ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊ ሥርዓቶች፣ ስለበጎ ፈቃደኝነት እና ስለ አገልግሎት ዋጋ እንዲሁም ስለ ቃለ-ዓዋዲውም ሆነ ሌሎች ቀኖናዊ መጻሕፍት በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ከተደረገ አገልግሎቱ ስሙር እና ውጤታማ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡

IMG-b56e0dc35774479c9ddfa5009e800139-V.j
IMG-ac3eb19c3fff1989ddb153639ac16819-V.j
ታዳጊ ወጣቶች
Youth

 

ወጣትነት ከሕፃንነት ወደ ዐዋቂነት በሚደረገው ሽግግር ወቅት
አንድን ሰው ለዐዋቂነት የሚያሸጋግሩ ስነልቦናዊ፣ አካላዊ፣
ማህበራዊና አዕምሮአዊ ለውጦች የሚከናዎኑበት ጊዜ ነው፡፡
በወጣትነት ዘመን ከውስጣዊ ፈተና በተጨማሪ ውጫዊ ፈተና
የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው፡፡ የተሻለ የዐዋቂነት ሕይወት
ለመምራት አንድ ወጣት እነዚህን ፈተናዎች በአሸናፊነት
መወጣት አለበት፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ ወሳኝ ሂደት
ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራት እሙን ነው፡፡ በዚህ መልኩ
ልጆቿን ኮትኩታ ባሉበት ፈታኝ ዘመን ፈተናውን ተቋቁመው ማለፍ
እንዲችሉ ማገዝ ከቻለች ለመንፈሳዊ ክብር ልታበቃቸው
ትችላለች፡፡ በምላሹም ከወጣቶች የሚጠበቀውን መጠነ-ሰፊ
አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡

ገዳማት
Monasteries

ገዳም ማለት ምድረ በደ ማለት ነው፡፡  በገዳም የእኔ የገሌ የሚሉት ንብረት የሌለበት ሁሉ በማህበር በአንድነት በጸሎት በሥራ እየተጉ ፍጹም የዓለምን ኃላፊነት ተረድተው የማታልፍ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዳለች በመገንዘብ ዘወትር በቀኖና ተወስነው የሚኖሩባት የቅዱሳን መኖሪያና ጸጋ እግዚአብሔር የማይለይበት ሲሆን በአንፃሩም ከሁሉ የከበደ የአጋንንት ጸር የሚበዛበት ቦታ ነው፡፡  ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት አስፈላጊ በመሆኑ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አርአያ ሆኖን በመገዳመ ቆሮንቶስ(በምድረ በዳ) ከዲያብሎስ የፈተን ዘንድ ተቀመጠ(ማቴ.4፡1-11)ፈታኝ ዲያቢሎስንም ድል አደረገው ገዳማዊ ሕይወትና ገዳም አስፈላጊ ሆኖ የመሠረተልን አምላካችን አርአያችን ኢየሰስ ክርስቶስ ነው፡፡  እኛም እርሱን በመከተል ገዳማዊ ሕይወት ለትሩፋት መሥሪያ፣ ለንስሐ ሕይወት መቆያ ለበረከት ለረድኤት አስፈላጊነቱን አምነን እንጠቀምበታለን፡፡

ገዳም.jpg
ላሊበላ 2.jpg
ላሊበላ 1.jpg
አክሱም.jpg
ሰላሴ ጎንደር.jpg
bottom of page