top of page

ክብረ መላእክት ቅዱሳን


በመምህር ኤፍሬም አሰፋ


፩) የመላእክት ተፈጥሮአቸው መላእክት በዕለተ እሑድ ከተፈጠሩ ፍጥረታት አንድ ክፍል ናቸው የመላእክት ተፈጥሮ እምኀበ አልቦ ነው መላእክት አንድ ጊዜ የተፈጠሩና በየጊዜው የማይባዙ ናቸው መላእክት በተፈጥሮአቸው ነባብያን፡ ለባውያን ፡ሕያውያን፡ ኃያላንም ናቸው።ሕማምና ሞት የለባቸውም፡ የመላእክት ቁጥር በአኃዝ አይወሰንም የብዙብዙ

ናቸው። መላእክት በነገድና በአለቃ ይከፈላሉ በነገድ መቶ በከተማ ዐሥር እንደነበሩ ይታወቃል።

አገልግሎታቸው _ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር የቅርብ አገልጋዮች ናቸው። ዘወትር በዙፋኑ ዙርያ ሆነው ያመሰግኑታል።(ራእ ፬-፰ ኢሣ ፮-፩) በተልእኮአቸውም ፈጣኖች ናቸው( መዝ 103:4 ዕብ ፩:፮) በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ፡ለተልእኮ ይወርዳሉ ይወጣሉ ለሰው ልጆችም ይራዳሉ( ዮሐ ፩:52 ,1 ,ዕብ1:14) የመላእክት ተልእኮ በጥቅሉ ሲገለጥ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል መላላክ፡ የሰውን ጸሎት ምጽዋትና ፡መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ


፪) የእግዚአብሔር ምህረት ና ቸርነት ወደሰዎች ማድረስ ነው።( ዳን9:20-22 ሉቃ 1:13 የሐዋ ፲:፫-፭)


፫) ሰዎች በሞቱ ጊዜ ነፍሶቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ያቀርባሉ።( ሉቃ 16:22 ዕዝ ሱቱ 6:6-20 )


፬) እያንዳንዱ ፍጥረት አዘውትረው ፡ይጠብቃሉ( ማቴ 18:10 ዳን 4:13)


፭) ለምሕረትም ለመዓትም ይላካሉ( ሮሜ 9:22)


፮) በመከራና በችግር ጊዜ ለተራዳኢነት ይላካሉ (የሐዋ 12 :7-11 መዝ 89:7)


፯) በፍጻሜ ዘመንም ፡ ይህ ዓለም በሚያልፍበት ጊዜ ይላካሉ ኃጥአንን ፡ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ24:31 ,ራእ7:1-4)

ይቀጥላል.......

168 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page