አማላጅነታቸው :- የቅዱሳን መላእክት አማላጅነትና ተራዳኢነት የሰዎችን ጸሎትና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ በተሰጣቸው ባለሟልነት ነዉ። በቅዱስ መጽሐፍ በሰፊው እንደምንረዳው የብዙዎችን ሰዎች ጸሎት መሥዋዕትና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር እያቀረቡ የሚፈልጉትን መልካም ነገር ሁሉ ያሰጣሉ። ደስታና የምስራች ሁሉ ለሰዎች ያበስራሉ። ደስታን ማብሠር ማጽናናትና የምስራችን መንገር ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ጸጋ ነው። ዘፍ 48:16 ዳን ፣ 10:10_12 _ሉቃ ፩፣፲፫ ሉቃ1:28_32 ይሁዳ ቁ _9። የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት በስፋት በቅዱሳት መጻሕፍት ይነገራል በተለይ በመጽሐፈ ሄኖክ 10:7 እና በዘካርያስ 1:12 ዘጸአ 23:20_23 መዝ 33:7 ላይ የተመለከቱት ጥቅሶች በግልጥ ያስረዳሉ። በተጨማሪ ቅዱሳን መላእክት ንስሐ ገብተው በተመለሱ ሰዎች ደስታ እንደሚያደርጉ በሉቃ 15:10 ተመዝግቦ እናነባለን ይህ ደግሞ ለሰው ልጆች ያላቸውን ፍቅርና አማላጅነት ያመለክታል። ክብራቸው :- ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ባለሟሎች ስለሆኑ ለአምላካቸው ቀናእያን ለነፍሳት ቀዋምያን ስለሆኑ ለምህረትም ለመዓትም ስለሚላኩ ሰዎችን በችግራቸው ጊዜ ስለሚረዱና ስለ ሚያማልዱ ቤተክርስቲያን ታከብራቸዋለች። በስማቸው ጽላት ቀርፃ ቤተክርስቲያን አሳንፃ ድርሳናቸውን አስጽፋ እንዲመሰገኑና እንዲከበሩ ታደርጋለች ፡የጸጋ የአክብሮት ስግደት እንዲሰገድላቸው ታስተምራለች። ዳን 8:15 _18 _ዘፍ22:31 ዘኁል 22:31 ኢያ5:13_15,።
ይቆየን
አማላጅነታቸው :- የቅዱሳን መላእክት አማላጅነትና ተራዳኢነት የሰዎችን ጸሎትና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ በተሰጣቸው ባለሟልነት ነዉ። በቅዱስ መጽሐፍ በሰፊው እንደምንረዳው የብዙዎችን ሰዎች ጸሎት መሥዋዕትና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር እያቀረቡ የሚፈልጉትን መልካም ነገር ሁሉ ያሰጣሉ። ደስታና የምስራች ሁሉ ለሰዎች ያበስራሉ። ደስታን ማብሠር ማጽናናትና የምስራችን መንገር ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ጸጋ ነው። ዘፍ 48:16 ዳን ፣ 10:10_12 _ሉቃ ፩፣፲፫ ሉቃ1:28_32 ይሁዳ ቁ _9። የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት በስፋት በቅዱሳት መጻሕፍት ይነገራል በተለይ በመጽሐፈ ሄኖክ 10:7 እና በዘካርያስ 1:12 ዘጸአ 23:20_23 መዝ 33:7 ላይ የተመለከቱት ጥቅሶች በግልጥ ያስረዳሉ። በተጨማሪ ቅዱሳን መላእክት ንስሐ ገብተው በተመለሱ ሰዎች ደስታ እንደሚያደርጉ በሉቃ 15:10 ተመዝግቦ እናነባለን ይህ ደግሞ ለሰው ልጆች ያላቸውን ፍቅርና አማላጅነት ያመለክታል። ክብራቸው :- ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ባለሟሎች ስለሆኑ ለአምላካቸው ቀናእያን ለነፍሳት ቀዋምያን ስለሆኑ ለምህረትም ለመዓትም ስለሚላኩ ሰዎችን በችግራቸው ጊዜ ስለሚረዱና ስለ ሚያማልዱ ቤተክርስቲያን ታከብራቸዋለች። በስማቸው ጽላት ቀርፃ ቤተክርስቲያን አሳንፃ ድርሳናቸውን አስጽፋ እንዲመሰገኑና እንዲከበሩ ታደርጋለች ፡የጸጋ የአክብሮት ስግደት እንዲሰገድላቸው ታስተምራለች። ዳን 8:15 _18 _ዘፍ22:31 ዘኁል 22:31 ኢያ5:13_15,። ይቆየን
በመምህር ኤፍሬም አሰፋ
Biruephy13@gmail.com
ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ና አምልኮ
Komentáre