top of page

ቅድስት ሥላሴ

Updated: May 19, 2020

ቅድስት ስላሴ ማለት ️

ሥላሴ ማለት ሦስትነት ማለት ሲሆን በልዩ አገላላጽ ሰለሠ ወይም ሦስት ሆነ ማለት ነው። ቅዱሳን

መጻሕፍትን መሰረት በማድርግ እግዚአብሔርን በአንድነትና በሦስትነት እናምነዋለን።

አንድነቱ፦በአገዛዝ፥በሥልጣን ይህን ዓለም በመፍጠርና በማሳለፍ፥በሕልውና፥በመለ



የመለኮት ባሕሪያት አንድ ሲሆን። ሦስትነት፦አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሲገለጽ፤

የአካል ሦስትነት፦ ለአብ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም አካል፥ፍጹም መልክ አለው፥ ለወልድም ፍጹም ገጽ፥ፍጹም

አካል፥ፍጹም መልክ አለው፥ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፥ፍጹም መልክ አለው።

የስም ሦስትነት፦አብ የአብ ስም ነው፥ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይጠሩበትም፥ወልድም የወልድ ስም ነው፥አብ መንፈስ ቅዱስ አይጠሩበትም፥መንፈስ ቅዱስም የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፥ አብ ወልድ አይጠሩበትም።

የግብር ሦስትነት፦የአብ ግብሩ ወልድን መውልድ መንፈስ ቅዱስን ማሥረጽ፥የወልድ ግብሩ፥ከአብ

መወለድ፥የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ ከአብ መሥረፅ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሰረጸ እንጂ ከወልድ አይደለም

፥ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም አያሰርጽም አይሰርጽም።

እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት፥ሦስት ሲሆን አንድ ነው። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ

ይባላል እንጂ ሦስት አማልክት አይባልም። አብ ውልድን ስለወለደ መንፈስ ቅዱስን ስላሰረጸ አይበልጣቸውም

አይቀድማቸውም።ይህንንም መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ያስረዳናል።

የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት[ዘፍ 1፡26]እግዚአብሔርም አለ፦ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር እግዚአብሔርም አለ ብሎ አንድነቱን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ሲል ደግሞ ብዛትን《ሶስትነት》ይገልጻል።

[ዘፍ 3፡22]እግዚአብሔር አምላክ አለ።እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ከእኛ የሚለውና እንደ አንዱ የሚለው እግዚአብሔር ከአንድ በላይ እንደሆነ የጠቁሙን ናቸው። [ዘፍ 11፡7] ኑ፥ እንውረድ አንዱ የአንድን ነገር

እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው ኑ የሚለው ቃል የሚያስረዳን አንዱ አካል ሌሎችን ሁለትና ከዚያም በላይ ሊሆን ይችላል መጥራቱን ነው [ዘፍ 18፡1-15] በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ድጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት ።ዓይኑንም አነሳና እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ድጃፍ

ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፤ እንዲህም አለ ፦ አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ።

[ኢሳ 6፡1-3] ቅዱስ፥ቅዱስ ፥ቅዱስ፥የሠራው ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር። አንዱ ቅዱስ ለአብ፥ሁለተኛው ቅዱስ ለወልድ፥ሦስተኛው ቅዱስ ለመንፈስ ቅዱስ መሆኑን ልብ እንበል ይህንን በድጋሜ

[ራዕ 4፡]እናገኘዋለን።

[ኢሳ 48፡16]አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

[ ማቴ 3፡16] ኢየሱስም ከተጠመቀ በኃላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፥እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፥እነሆም ፥ድምፅ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

[ማቴ 28፡19] እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፥እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድርስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

[ሉቃ 1፡35]መንፈስ ቅዱስ በአንች ላይ ይመጣል፥የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ሰለዚህ ደግሞ ከአንች የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጂ ይባላል። [ዮሐ 14፡25]

ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህንን ነግሬአችኋለሁ፥አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። [1ኛ ቆሮ 12፡3]ስለዚህም ማን በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፥ኢየሱስ ጌታ ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።

[2ኛ ቆሮ 13፡14]የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!

ወስብሓት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክብር አሜን





#ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #Ethiopian #Ethiopian orthodox Tewahedo Church

571 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page